Saturday, July 11, 2009

The unpredicted nature of the issue is proved. So let us wait filled with hope that the fathers will come up with a decision which will glorify the church after the Holy Spirit.

2 comments:

Anonymous said...

What is the update on July,13?

Anonymous said...

የጥንተ-ጠላታችን መርዝ የመጨረሻ ቅምሻ?

የዘመደ-እጓለመሕያው/የትዝምደ-ሰብእ/የደቂቀ-አዳም/የውሉደ-ሔዋን/የሰው ዘርዕ በሙሉ (humankind’s/humanity’s) የጥንት-ጥንት ጠላታችን እኛ ኢትዮጵያውያን ሰይጣን/ዲያብሎስ፤ ዕብራውያን “ሳጣን፣” ዐረቦች “ሾይጣን”/“ኢብሊስ፣” ጽርአውያን “ዲያቦሎስ” እንግልጣሮቹሙ Satan/Devil የሚሉት ከሳሽ፣ አሳጭ፣ አሳሳች፣ በጦር በነገር የሚከታተል ባላጋራ፣ ወደረኛ ክፉ መልአክ ሳጥናኤል ነው።

እንደ-ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በተለይ ከ16ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ወዲህ ጥንተ-ጠላታችን ኾና የተነሣችብን ተንኮለኛ ወደረኛ የኮተሊክ ቤተክሲያን ናት። ይኸውም ሊታወቅ በፈረጠመ ጡንቻዋ በየጊዜው መርዟን ልትግተን ሞክራለች። ከከንፈራችን አልፋ ከጉረሯችን ብታደርሰውም እኛ ግን ባለመዋጣችን አልሞትንላትም። የጉልበቱ ባይሳካላት ዛሬ ደግሞ መርዙን ማር አስመስላ በገዛ እጃችን (በነአባ ገብርኤል፣ በነአባ ሙሴ፣ ይልቁንም የዘር ፖለቲካ በነእጨጌ በትረ-ጊዮርጊስ መዐርግ ባስቀመጣቸው በነአባ ጳውሎስ ልታውጠን በምላሷ እያግባባችን፣ በገንዘቧ እያባበለችን ትገኛለች። (በነአባ ገብርኤል ላልኩት፦ የኹለት ባሕርይ ትምርታቸውን የቀረሹበትን መጽሐፍ እናስታውስ፤ በነአባ ሙሴ ለሚለውም፦ በሊቃውንት ተርታ ስም-የለሹ ይኸ ደግሞ አዲግራት ያደረጉትን ማስታወስ በቂ ነው፤ ይልቁንም የዘር ፖለቲካ በነእጨጌ በትረ-ጊዮርጊስ መዐርግ ባስቀመጣቸው በነአባ ጳውሎስ ያልኩበት ምክንያት፦ እጨጌ ዘመንበረ-ተክለሃይማኖት ተብየው “ወረከብናሁ ለበትር ዘይቀጠቅጣ ለሮሜ፤ ጽሩበ በንባብ ወቅሩፀ በትርጓሜ” የተባለላቸው እጨጌ በትረ-ጊዮርጊስ በተቀመጡበት መንበር ተዘርፍጠው፦ እምየ የልብ ዐይናማው አለቃ አያሌው ታግለው ባያስቀሩት ኖሮ፤ የኮተሊክን ቤተክሲያን ሥራት እንዳለ ሕግ አድርገው ሊጭኑብን መሞከራቸውን አባ ገብርኤል ሳይቀሩ ለግል ጠባቸው ማዳመቂያ ሲሉ ነግረውናል። እንዲህ ያለ ዐይነተኛ የሥራት ለውጥ ለማምጣት መሻታቸው በዕውር ልባቸው ተደብቆ ያለ የውሳኔ-ሃይማኖት [የዶግማ] ችግር መኾኑ ግልጥ ነው። የሥራት ለውጥ ነው የተባለውም ቢኾን በቀጥታ ሃይማኖትን የሚነካ መነበሩን የተረዱት አለቃ፦ የመንፈስቅዱስን ድርሻ ልውሰድ የሚል ሰው “ጣዖት” መኾኑን በሚገባ ጠቁመውን ነበር፤ የሰማቸው ጠፋ እንጀ። ኹሉም “ዘከርስ” እንጂ “ዘመንፈስ ቅዱስ” ስላልነበረ።)

አሁን ታዲያ፦ አባቶች ተብየዎቹ በነአባ ጳውሎስ እጅ እንደመድኀኒት ካልጠጣችኋት ተሞታላቸኹ እየተባሉ የሚጋበዙትን የጥንተ-ጠላታችን የኮተሊክ ቤተክሲያን ብሎም የጥንት-ጥንት ጠላታችን የዲያብሎስን ግብዣ “እንብየ” ብለው ተፍተው ቤተክርስቲያናችንን ይታደጓት ይኾን??? እንዲህ ካደረጉ በአምላከ-ኢትዮጵያ ቸርነት ይኸ የመጨረሻ ቅምሻ ይኾናል ብየ ተስፋ አደርጋለኹ። አለዚያ ግን…አዪ… እንጃልን?